Uppskattad leveranstid 7-12 arbetsdagar
Fri frakt för medlemmar vid köp för minst 249:-
ምስሌን ፍለጋ የተሰኘው ልብወለድ+ከፊል ግለ ታሪክ+የስብዕና እድገትን በአንድ የያዘው የተለያየ የድሜ ክልል ላይ ያሉ ሰዎች በተለይ ወጣቶች ቢያነቡ ብዙ የሚያተርፉበት መፅሀፍ ነው። መጽሐፉን አንጋፋ የስነ-ጽሑፍ ባለሞያዎች በአርትኦት እንዲሁም በመገምገም እና አስተያየት በመስጠት ተሳትፈውበታል። ደራሲዋ ስለመጽሐፉ እንደዚህ ትላለች ....
"በዚህ መጽሐፍ ውስጥ እኔን(ሐና ኃይሉን) በትናንት ትዝታዬ እና በነገ ምናቤ መሀል አስቀምጬ በፈጠርኳቸው የልቦለድ ታሪኮች ውስጥ ታገኙኛላችሁ። ይህ መጽሐፍ ትናንትናዬን የታዘብኩበት ነገዬን ደግሞ በምናቤ ያስተዋልኩበት ሁነኛ ሰነዴ ነው ብዬ አምናለሁ።
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በምናብ የተፈጠሩ አስደናቂ ሰዎች ያሉትን ያህል፣ በትናንት ትዝታዬ ውስጥ በሕይወቴ የነበሩ፣ አሁንም ያሉ ሰዎች ይገኙበታል።
ይህን መጽሐፍ "ምስሌን ፍለጋ" ብዬ እንድሰይመው ያደረገኝ ዋነኛ ምክንያት፣ እንደሚታወቀው ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ፈጣሪ የሰውን ልጅ በአምሳሉ እንደፈጠረው ተገልጿል። መጀመሪያ የተፈጠርንበት ምስል ማለት፣ ከፈጣሪ የተሰጠን ሙሉ ዐቅም፣ ንጽሕና፣ ጥበብ እና ዕውቀት የመሳሰሉት በሙሉ ሆነ በከፊል የማንነታችን መገለጫዎች ናቸው።
ሥዕሉን አይታችሁ ሠዓሊውን
- Format: Pocket/Paperback
- ISBN: 9798224197996
- Språk: Amhariska
- Antal sidor: 298
- Utgivningsdatum: 2024-05-15
- Förlag: Kulu1.com